አሞፅ
በግምት ከ፯፻፺፪ እስከ ፯፻፵ ም.ዓ. በአይሁድ ንጉስ ኡዝያ እና በእስራኤል ንጉስ ኢዮርብዓም ዘመናት የተነበየ የብሉይ ኪዳን ነቢይ።
ትንቢተ አሞፅ
የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ የአሞፅ ትንቢያት እስራኤልን እና ጎረቤቷ አገሮችን ወደ ጽድቅ እንዲመለሱ አስጠንቅቀዋል።
ምዕራፍ ፩–፭ እስራኤልን እና ጎረቤቷ አገሮችን ንስሀ እንዲገቡ ይጠራሉ። ምዕራፍ ፭ ጌታ ምስጢሮቹን ለነብያቱ እንደሚገልፅ እና በመተላለፍ ምክንያት እስራኤል በጠላት እንደምትደመሰስ ያስረዳል። ምዕራፍ ፮–፰ አሶር ከመውረሯ ከብዙ አመቶች በፊት ስለእስራኤል መውደቅ ተነበየ። ምዕራፍ ፱ እስራኤል ወደምድሯ ዳግማ እንደምትመለስ ተነበየ።