የጥናት እርዳታዎች
ሰማርያ


ሰማርያ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የሰሜን እስራኤል መንግስት ዋና ከተማ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፳፫–፳፬)። በኮረብታ ላይ በነበራት ጠንካራ ወታደራዊ ቦታ፣ አሶር እስከ ሶስት አመት በጦር ከበባ ድረስ እርሷን ለመያዝ አልቻሉም ነበር (፪ ነገሥ. ፲፯፥፭–፮)። ሄሮድስ እንደገና ገነባት እና ሰባስቴ ብሎ ጠራት። በአዲስ ኪዳን ጊዜ ውስጥ፣ ሰማርያ በዮርዳኖስ በስተምዕራብ ለሚገኘው የፍልስጥኤም አውራጃ በሙሉ የተሰጠ ስም ነው።