የጥናት እርዳታዎች
አዲስ እና የዘለአለም ቃል ኪዳን


አዲስ እና የዘለአለም ቃል ኪዳን

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት (ት. እና ቃ. ፷፮፥፪)። ከክህደት ጊዜ በኋላ እንደ አዲስ በሚገለጽበት ጊዜ ሁሉ አዲስ ነው። ይህም ዘለአለማዊ የሚሆነው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለሆነና ሰዎች ይህን ለመቀበል ፈቃደኛ በሆኑበት በእያንዳንዱ የወንጌል ዘመን ይደሰቱበት የነበረ ስለሆነ ነው። አዲሱ እና የዘለአለም ቃል ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል እንደገና በምድር ላይ ለሰዎች ተገለጸ። ይህም በክህነት ስልጣን በኩል የሚከናወኑ ለሰው ደህንነት፣ ህያውነት፣ እና ዘለአለማዊ ህይወት ዝግጅት የሚያቀርቡ እንደ ጥምቀት እና የቤተመቅደስ ጋብቻ አይነት ቅዱስ ስነስርዓቶችን የያዘ ነው። ሰዎች ወንጌልን ሲቀበሉ እና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለማክበር ቃል ሲገቡ፣ እግዚአብሔር የአዲስ እና የዘለአለም ቃል ኪዳን በረከቶችን ለእነርሱ ለመስጠት ቃል ኪዳን ይገባል።