ቀዳሚ አመራር ደግሞም ራዕይ; የክህነት ቁልፎች; ፕሬዘደንት ተመልከቱ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንትና አማካሪዎቹ እነርሱ ቤተክርስቲያኗን በሙሉ የሚመሩ የሶስት ሊቀ ካህናት ቡድን ናቸው። ቀዳሚ አመራር የክህነት ቁልፎችን በሙሉ ይዘዋል። የመንግስት ቁልፎች ሁልጊዜም የሊቀ ካህን አመራር ናቸው, ት. እና ቃ. ፹፩፥፪. የሊቀ ካህናት አመራር በሁሉም ሀላፊነቶች የማስተዳደር መብት አላቸው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፱፣ ፳፪. ቃሌን የሚቀበል ማንኛውም የቀዳሚ አመራርን ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፻፲፪፥፳፣ ፴. ቀዳሚ አመራር ለቤተክርስቲያኗ የእግዚአብሔርን ቃላት (ራዕዮች) ይቀበላሉ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፳፮.