ንጹህነት ደግሞም ማመንዘር; ስሜታዊ፣ ስሜታዊነት; በጎነት; ዝሙት መፈጸም ተመልከቱ የወንዶች እና የሴቶች ወሲባዊ ንጹህነት። ዮሴፍ የጲጥፋራ ሚስትን መገፋፋት ተቋቋመ, ዘፍጥ. ፴፱፥፯–፳፩ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፬; ፶፱፥፮). አታመንዝር, ዘፀአ. ፳፥፲፬. ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት, ምሳ. ፲፪፥፬ (ምሳ. ፴፩፥፲). ሥጋችሁ … የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን, ፩ ቆሮ. ፮፥፲፰–፲፱. በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን, ፩ ጢሞ. ፬፥፲፪. ማንኛውም እርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖር አይቻለውም, ፩ ኔፊ ፲፥፳፩. እኔ ጌታ አምላክ በሴቶች ንጹህነት እደሰታለሁ, ያዕቆ. ፪፥፳፰. ወሲባዊ ኃጢያት እርኩሰት ነው, አልማ ፴፱፥፩–፲፫. ድንግልነት እና ምግባረ ጥሩነት ከሁሉም ነገሮች በላይ የተወደሰና ውድ ናቸው, ሞሮኒ ፱፥፱. በንጹህነት እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፫.