ትንቢት፣ መተንበይ
ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ራዕይ በኩል ሰው የሚቀበላቸው በመለኮታዊ የተነሳሱ ቃላት ወይም ፅሁፎችን የያዘ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነው (ራዕ. ፲፱፥፲)። ትንቢት ስላለፈው፣ ስለአሁኑ፣ ወይም ወደፊት ስለሚመጣው ነገር ግንኙነት ያለው ነው። ሰው ሲተነብይ፣ ለእራሱ ጥቅም ወይም ለሌሎች ጥሩ ጥቅም እግዚአብሔር እንዲያውቅ የሚፈልገውን ይናገራል ወይም ይፅፋል። ግለሰቦች ትንቢቶችን ወይም ራዕዮችን ለእራሳቸው ህይወት ለመቀበል ይችላሉ።