ላማናውያኑ ሳሙኤል በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ከአዳኝ መወለድ በፊት ኔፋውያንን እንዲያስተምር እና እንዲያስጠነቅቅ በጌታ የተላከ ላማናውያን ነቢይ። ሳሙኤል ከኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ እና መሞት ጋር ግንኙነት ስላላቸው ምልክቶች እና ስለኔፋውያን ጥፋት ተነበየ (ሔለ. ፲፫–፲፮)።