አንድነት ደግሞም እግዚአብሔር፣ አምላክ ተመልከቱ በሀሳብ፣ በፍላጎት፣ እና በአላማ በመጀመሪያ ከሰማይ አባታችንና ከኢየሱስ ጋር፣ እና ከእዚያም ከሌሎች ቅዱሳን ጋር አንድ መሆን። ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው, መዝ. ፻፴፫፥፩. እኔና አብ አንድ ነን, ዮሐ. ፲፥፴ (ት. እና ቃ. ፶፥፵፫). ኢየሱስ እርሱ እና አባቱ አንድ እንደሆኑ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ጸለየ, ዮሐ. ፲፯፥፲፩–፳፫ (፫ ኔፊ ፲፱፥፳፫). ሁላችሁ የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን እለምናችኋለሁ, ፩ ቆሮ. ፩፥፲. በአንድ ሀሳብና በአንድ ልብ ሁኑ፣ በሁሉ ነገሮች ተስማሙ, ፪ ኔፊ ፩፥፳፩. ቅዱሳን ልባቸው በአንድ ላይ በአንድነት ይጣበቁ, ሞዛያ ፲፰፥፳፩. ኢየሱስ በኔፋውያን ደቀ መዛሙርት መካከል አንድነት እንዲኖር ጸለየ, ፫ ኔፊ ፲፱፥፳፫. ደቀ መዛሙርቱ በብርቱ ፀሎታቸው እና ፆማቸው አንድ ሆነው ነበር, ፫ ኔፊ ፳፯፥፩. አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ ናቸው, ት. እና ቃ. ፳፥፳፯–፳፰ (ት. እና ቃ. ፴፭፥፪; ፶፥፵፫). ከእውነት ቤተክርስቲያን ጋር አንድ መሆን ሀላፊነታችሁ ነው, ት. እና ቃ. ፳፫፥፯. እንደ ትእዛዜ በጸሎት አንድ ሆናችሁ በእምነት የምትጠይቁትን ማንኛውንም ትቀበላላችሁ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፮. አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም, ት. እና ቃ. ፴፰፥፳፯. እነርሱ የአንድ ልብ እና የአንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው, ሙሴ ፯፥፲፰.