ማስተዋል ደግሞም እውቀት; እውነት; ጥበብ ተመልከቱ እውቀትን ማግኘት ወይም በህይወት እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከማወቅ በተጨማሪ፣ የአንዳንድ እውነትን ትርጉም መገንዘብ። በራስህም ማስተዋል አትደገፍ, ምሳ. ፫፥፭. ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ, ምሳ. ፬፥፯. ኢየሱስ በምሳሌ ተናገረ እናም አንዳንዱ አልገባቸውም, ማቴ. ፲፫፥፲፪–፲፯. ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው, ሉቃ. ፳፬፥፵፭. እነዚህን ቃላት መረዳት ካልቻላችሁ፣ ይህም ስላልጠየቃችሁ, ፪ ኔፊ ፴፪፥፬ (፫ ኔፊ ፲፯፥፫). መዝገቦቹ የተጠበቁት እንድናነባቸው እና እንድናስተውላቸው ነው, ሞዛያ ፩፥፪–፭. ባለማመናቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሊረዱት አልቻሉም ነበር, ሞዛያ ፳፮፥፫. ትክክለኛ ማስተዋል የነበራቸው, አልማ ፲፯፥፪–፫. ቃሉ ግንዛቤዬን ያበራልኝ ጀምሯል, አልማ ፴፪፥፳፰. እንዲገባችሁም እንወቃቀስ, ት. እና ቃ. ፶፥፲–፲፪፣ ፲፱–፳፫. ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስተውሉ አስተምሯቸው, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፭. የእግዚአብሔር ስራዎች እና ሚስጥሮች ለመገባት የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፻፲፬–፻፲፮. ይጣን ልቦቻቸውን ከእውነቱ ለማዞር ይፈልጋል, ት. እና ቃ. ፸፰፥፲. የክርስቶስ ብርሀን የምትረዱበትን ያነሳሳል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፩.