የእግዚአብሔር ቃል ደግሞም ራዕይ; ቅዱሳት መጻህፍት; የእግዚአብሔር ትእዛዛት ተመለከቱ መመሪያዎች፣ ትእዛዛት፣ ወይም ከእግዚአብሔር የመጣ መልእክት የእግዚአብሔር ልጆች ቃሉን በመንፈስ በኩል በቀጥታ ራዕይ ወይም በተመረጡት አገልጋዮቹ መቀበል ይችላሉ (ት. እና ቃ. ፩፥፴፰)። ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል, ዘዳግ. ፰፥፫ (ማቴ. ፬፥፬; ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፫–፵፬). ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው, መዝ. ፻፲፱፥፻፭. በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ, የሐዋ. ፬፥፴፩–፴፫. የብረት በትር የእግዚአብሔር ቃል ነው, ፩ ኔፊ ፲፩፥፳፭ (፩ ኔፊ ፲፭፥፳፫–፳፭). እናንተ ደንዝዛችኋል፣ ስለዚህ ቃሉ ሊሰማችሁ አልቻለም, ፩ ኔፊ ፲፯፥፵፭–፵፮. የእግዚአብሔርን ቃል ለማይቀበል ለዚያ ሰው ወዮለት, ፪ ኔፊ ፳፯፥፲፬ (፪ ኔፊ ፳፰፥፳፱; ኤተር ፬፥፰). የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እስከመጨረሻው በመፅናት ቀጥሉ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፳ (፪ ኔፊ ፴፪፥፫). ባለማመናቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሊረዱት አልቻሉም ነበር, ሞዛያ ፳፮፥፫ (አልማ ፲፪፥፲). የእግዚአብሔርን ቃል ያውቁ ዘንድ ቅዱሳን መጻሕፍትን በትጋት አጥንተዋል, አልማ ፲፯፥፪. የእግዚአብሔር ቃል በጎነት ሞክሩ, አልማ ፴፩፥፭. አልማ የእግዚአብሔርን ቃል ከዘር ጋር አነጻጸረ, አልማ ፴፪፥፳፰–፵፫. በመንፈስ ቅዱስ ሲነሳሱ የሚናገሩት ማንኛውም ነገር ቅዱሣት መጻህፍት ናቸው, ት. እና ቃ. ፷፰፥፬. ከእግዚአብሔር አፍ ከሚመጣው እያንዳንድ ቃልም ትኖራላችሁ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፬–፵፭. ቃላቶቼን እንደሀብት የሚያከማቸው ማንም አይታለልም, ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፴፯.