አስጸያፊ፣ አስከፊ፣ አሰቃቂ፣ ርኩሰት ደግሞም ኃጢያት ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ለጻድቅ እና ንጹሁ ጽያፌ እና ጥላቻ የሚያመጣ። ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው, ምሳ. ፲፪፥፳፪. ኩራት በጌታ ፊት የርኩሰት ነው, ያዕቆ. ፪፥፲፫–፳፪. ክፉዎች በራሳቸዉ እርኩሰት ሁኔታ ይመደባሉ, ሞዛያ ፫፥፳፭. ንጹህ አለመሆን ደም ከማፍሰስ ወይንም መንፈስ ቅዱስን ከመካድ በቀር ከሌሎች ኃጢአቶች ሁሉ ይበልጥ አስከፊ ነው, አልማ ፴፱፥፫–፭. የጌታ ቁጣ በርኩሰታቸው ላይ ተቀጣጥሏልና, ት. እና ቃ. ፺፯፥፳፬.