እርግማን፣ እርግማኖች
በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ እርግማን ጻድቅ ባለመሆን ምክንያት በነገሮች፣ በሰዎች፣ ወይም በህዝቦች ላይ ፍርዶችንና የእነዚህን ውጤቶች ሚያመጣን መለኮታዊ ህግ መጠቀም ማለት ነው። እርግማኖች የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅርና ፍተህ መግለጫ ነው። እነዚህም በእግዚአብሔር እራሱ የሚነገሩ ወይም በባለስልጣን አገልጋዮቹ የሚታወቁ ናቸው። አንዳንዴ፣ የእርግማኑ ሙሉ ምክንያት የሚታወቁት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። በተጨማሪም፣ የተረገመ ሁኔታ የሚያጋጥማቸው እግዚአብሔርን በፈቃደኝነት በማይታዘዙት ነው እና በዚህም ከእግዚአብሔር መንፈስ እራሳቸውን ያርቃሉ።
ግለሰቦች ወይም ህዝቦች በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነትና ለወንጌሉ ህግጋትና ስነስርዓቶች ታዛዥነታቸው ምክንያት ጌታ እርግማንን ለማንሳት ይችላል (አልማ ፳፫፥፲፮–፲፰፤ ፫ ኔፊ ፪፥፲፬–፲፮፤ እ.አ. ፩፥፫)።
ስድበት
እርግማን የብልግና፣ የስድብ፣ ወይም የንቀት ቋንቋን መጠቀም ነው።