አክዓብ ደግሞም ኤልዛቤል ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የሰሜን እስራኤል ከሁሉም በላይ ክፉ እና ሀይለኛ ንጉስ ከሆኑት አንዱ። የሲዶንን ልዕልት ኤልዛቤልን አገባ፣ በእርሷም ተፅዕኖ በኩል የበኣልን እና የአስታሮት ማምለክን በእስራኤል ውስጥ መሰረተ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፳፱–፴፫፤ ፪ ነገሥ. ፫፥፪) እና ነብያትን እና ያህዌህን ማምለክ ለማስወገድ ጥረት ተደርጎ ነበር (፩ ነገሥ. ፲፰፥፲፫)። በእስራኤል ላይ በሰማሪያ ሀያ ሁለት ዓመት ነገሠ, ፩ ነገሥ. ፲፮፥፳፱ (፩ ነገሥ. ፲፮–፳፪). ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ ይልቅ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ, ፩ ነገሥ. ፲፮፥፴. በጦርነትም ተገደለ, ፩ ነገሥ. ፳፪፥፳፱–፵.