የእግዚአብሔር መንግስት ወይም መንግስተ ሰማያት
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር የምትገኘው የእግዚአብሔር መንግስት ናት (ት. እና ቃ. ፷፭)። የቤተክርስቲያኗም አላማ አባሏን በሰለስቲያል መንግስት ወይም በመንግስተ ሰማያት ውስጥ በዘለአለም ለመኖር ለማዘጋጀት ነው። ነገር ግን፣ ቅዱሣት መጻህፍት አንዳንዴ ቤተክርስቲያኗን እንደ መንግስተ ሰማያት ይጠሯታል፣ ይህም ቤተክርስቲያኗ በምድር የምትገኝ መንግስተ ሰማያት ናት ማለት ነው።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር የምትገኝ የእግዚአብሔር መንግስት ናት፣ ነገር ግን ይህች በዚህ ጊዜ በመንፈሳዊ መንግስት የተገደበች ናት። በአንድ ሺህ አመት፣ የእግዚአብሔር መንግስት የፖለቲካና የመንፈስ መንግስት ትሆናለች።