የጥናት እርዳታዎች
የዮርዳኖስ ወንዝ


የዮርዳኖስ ወንዝ

የዮርዳኖስ ወንዝ ከገሊላ ባህር ወደ ሙት ባህር ይፈሳል። ወንዙ ፻ ማይል (፻፷ኪሎ ሜትር) የረዘመ ነው እናም ከአርሞንዔም ተራራ ከሚመነጩ መንጮች የተሰራ ነው። ይህም በእስራኤል ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ወንዝ ነው።

ከዚህ ወንዝ ጋር የተገናኙ ሁለት አስፈላጊ ድርጊቶች እስራኤል እንድትሻገር ጌታ ወንዙን በሁለት መክፈሉ (ኢያ. ፫፥፲፬–፲፯) እና የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ ነበሩ (ማቴ. ፫፥፲፫–፲፯፩ ኔፊ ፲፥፱)።