ላማን ደግሞም ላማናውያን; ሌሂ፣ የኔፊ አባት ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የሌሂና የሳሪያ የመጀመሪያ ልጅ እናም የኔፊ ታላቅ ወንድም (፩ ኔፊ ፪፥፭)። ላማን ጥሩ ከማድረግ በብዙ ጊዜ መጥፎዎችን ለማድረግ መረጠ። ላማን በአባቱ ላይ አጉረመረመ, ፩ ኔፊ ፪፥፲፩–፲፪. በጻድቅ ወንድሙ በኔፊ ላይ አመጸ, ፩ ኔፊ ፯፥፮ (፩ ኔፊ ፫፥፳፰–፳፱). በሌሂ ራዕይ ውስጥ ከህይወት ዛፍ ፍሬ አልበላም, ፩ ኔፊ ፰፥፴፭–፴፮. እርግማን በላማንና በእርሱ ተከታዮች ላይ መጣ, ፪ ኔፊ ፭፥፳፩ (አልማ ፫፥፯).