ካም ደግሞም ኖኅ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ የአባቶች አለቃ ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የኖህ ሶስተኛ ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፭፥፴፪፤ ፮፥፲፤ ሙሴ ፰፥፲፪፣ ፳፯)። ኖህ፣ ወንድ ልጆቹ፣ እና ቤተሰቦቻቸው ወደ መርከቡ ገቡ, ዘፍጥ. ፯፥፲፫. የካም ልጅ ከነዓን ተረገመ, ዘፍጥ. ፱፥፲፰–፳፭. የካም መንግስት ከአባት ወደ ወንድ ልጅ የሚተላለፍ ነበር እናም በምድራዊ ነገሮችና በጥበብ ቢባረክም በክህነት ስልጣን የተባረከ አልነበረም, አብር. ፩፥፳፩–፳፯. የካም ባለቤት፣ ግብፅዎስ፣ የቃየን ትውልድ ነበረች፣ የሴት ልጃቸው ግብፅዎስ ወንድ ልጆች በግብፅ ውስጥ ሰፈሩ, አብር. ፩፥፳፫፣ ፳፭ (መዝ. ፻፭፥፳፫; ፻፮፥፳፩–፳፪).