መፈወስ፣ ፈውሶች ደግሞም ለታመሙት አገልግሎት መስጠት; መቀባት ተመልከቱ እንደገና በስጋ እናም በመንፈስ ደህና ማድረግ ወይም ጤና መስጠት። ቅዱሣት መጻህፍት የጌታንና የአገልጋዮቹን ተአምራት ፈውሶች ብዙ ምሳሌዎችን የያዙ ናቸው። እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ, ዘፀአ. ፲፭፥፳፮. ናዕማን እራሱን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ለሰባት ጊዜ ጠለቀ እናም ተፈወሰ, ፪ ነገሥ. ፭፥፩–፲፬. በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን, ኢሳ. ፶፫፥፭ (ሞዛያ ፲፬፥፭). የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል, ሚል. ፬፥፪. ኢየሱስ ህማምን ሁሉ ፈወሰ, ማቴ. ፬፥፳፫ (ማቴ. ፱፥፴፭). ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው, ማቴ. ፲፥፩. ልባቸው የተሰበረውም እንድፈውስ ልኮኛል, ሉቃ. ፬፥፲፰. እነርሱም በእግዚአብሔር በግ ኃይል ተፈወሱ, ፩ ኔፊ ፲፩፥፴፩. በክርስቶስ ቤዛነት ካመንህ መፈወስ ትችላለህ, አልማ ፲፭፥፰. እርሱም እያንዳንዳቸውን ፈወሳቸው, ፫ ኔፊ ፲፯፥፱. ለመፈውስ በእኔ እምነት ያለው ይፈወሳል, ት. እና ቃ. ፵፪፥፵፰. በስሜም የታመሙትን ይፈውሳሉ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፷፰. በመፈወስ ስጦታዎችም እናምናለን, እ.አ. ፩፥፯.