ሞዛያ፣ የቢንያም አባት ደግሞም ቢንያም፣ የሞዛያ አባት; ዛራሔምላ ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ በዛራሔምላ ህዝብላይ ንጉስ እንዲሆን የተደረገ የኔፋውያን ነቢይ። ከኔፊ ምድር እንዲወጣ ተጠነቀቀ, ኦምኒ ፩፥፲፪. የዛራሔምላ ህዝብን አገኘ, ኦምኒ ፩፥፲፬–፲፭. የዛራሔምላ ህዝብ የእርሱን ቋንቋ እንዲማሩ አደረገ, ኦምኒ ፩፥፲፰. በአንድነት የተዋሃዱ ህዝብ ንጉስ እንዲሆን ተመደበ, ኦምኒ ፩፥፲፱. ከሞተ በኋላ፣ ልጁ ቢንያም በምትኩ ነገሰ, ኦምኒ ፩፥፳፫.