የጥናት እርዳታዎች
ስምዖን


ስምዖን

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የያዕቆብ እና የልያ ሁለተኛ ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፳፱፥፴፫፴፭፥፳፫ዘፀአ. ፩፥፪)። ሴኬማውያንን በመግደል ከሌዋ ጋር ተባበረ (ዘፍጥ. ፴፬፥፳፭–፴፩)። በዘፍጥረት ፵፱፥፭–፯ ውስጥ ስምዖንን በተመለከተ የያዕቆብ ትንቢት ይገኛል።

የስምዖን ጎሳ

የስምዖን ትውልዶች በብዙ ጊዜ ከይሁዳ ጎሳ ጋር በይሁድ መንግስት ድንበር ውስጥ ይኖሩ ነበር (ኢያ. ፲፱፥፩–፱፩ ዜና ፬፥፳፬–፴፫)። የስምዖን ጎሳ ከይሁዳ ጋር በመተባበር ከከነዓናውያን ጋር ተዋጉ (መሳ. ፩፥፫፣ ፲፯)። በኋላም የዳዊት ሰራዊት አባል ሆኑ (፩ ዜና ፲፪፥፳፭)።