አስተዳደሪያዊ አዋጅ ፩
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች በመጨረሻ ገጾች ላይ የታተሙት፣ የአስተዳደሪያዊ አዋጅ ፩ የመጀመሪያ ክፍል መግለጫም ተብሎ ይታወቃል። የተሰጠውም በፕሬዘደንት ውልፈርድ ውድሩፍ ነበር እናም በጥቅምት ፮፣ ፲፰፻፺ (እ.አ.አ.) በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ለቤተክርስቲያኗ አባላት ቀረበ። ከ፲፰፻፷፪ (እ.አ.አ.) ጀምሮ፣ የተለያዩ ህግጋት በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባትን ህገወጥ አደረጉት። ጌታ በራዕይ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባትን ካላቆሙ በቅዱሳን ላይ ምን እንደሚደርስ ለውልፈርድ ውድሩፍ አሳየ። መግለጫው ከአንድ ሚስት በላይ ማጋባት እንደቆመ ማስታወቂያ ሰጠ።