በጎነት ደግሞም ሀይል; ቅንነት; ንጹህነት ተመልከቱ ታማኝነት እና በስነምግባር በጣም ጥሩነት፣ ሀይል እና ጥንካሬ (ሉቃ. ፰፥፵፮)፣ ወይም ወሲባዊ ንጹህነት (ሞሮኒ ፱፥፱)። ምግባረ መልካም ሴት ነሽ, ሩት ፫፥፲፩. ንጹህ እጅ እና ንጹህ ልብ ያለው በጌታ ቅዱስ ቦታ ላይ ይቆማል, መዝ. ፳፬፥፫–፬. ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት, ምሳ. ፲፪፥፬. የምግባረ ጥሩ ሴት ዋጋ ከቀይ ዕንቁ በላይ ታላቅ ነው, ምሳ. ፴፩፥፲–፴፩. በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ, ፪ ጴጥ. ፩፥፭ (ት. እና ቃ. ፬፥፮). የእግዚአብሔር ቃል በጎነት ሞክሩ, አልማ ፴፩፥፭. ምግባረ ጥሩነትም ሀሳብህን ያሳምር, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፭. ምግባረ ጥሩ በመሆን እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፫ (ፊልጵ. ፬፥፰).