እረፍት ደግሞም ሰላም; የሰንበት ቀን ተመልከቱ ከአስቸጋሪ ሀሳብ እና ብጥበጣ በሰላምና በነጻነትን መደሰት። ጌታ በእዚህ ህይወት ጊዜ ለታማኝ ተከታዮቹ እንዲህ አይነት እረፍት እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል። ለእነርሱም በሚቀጥለው ህይወት የእረፍት ቦታ አዘጋጅቶላቸዋል። እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ, ዘፀአ. ፴፫፥፲፬. እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ, ማቴ. ፲፩፥፳፰–፳፱. ወደ እረፍቱም ይገቡ ዘንድ በትጋት ሠራን, ያዕቆ. ፩፥፯ (ዕብ. ፬፥፩–፲፩). ንስሃ የሚገቡ በእረፍቴ ይገባሉ, አልማ ፲፪፥፴፬. ንጹህ የሆኑ፣ እናም ወደ ጌታ እረፍት የገቡ በጣም ብዙ ነበሩ, አልማ ፲፫፥፲፪–፲፮. ገነት የእረፍት ቦታ ናት, አልማ ፵፥፲፪ (አልማ ፷፥፲፫). በደሜ ልብሳቸውን ካጠቡት በስተቀር በእረፍቱ የሚገባ ማንም የለም, ፫ ኔፊ ፳፯፥፲፱. ከእነሱ ጋር በአባቴ መንግስት አብረህ ታርፍ ዘንድ ለዚህ ህዝብ ንስሃን አውጅ፣ አሜን, ት. እና ቃ. ፲፭፥፮ (ት. እና ቃ. ፲፮፥፮). የሞቱትም ከሁሉም ስራዎቻቸው ያርፋሉ, ት. እና ቃ. ፶፱፥፪ (ራዕ. ፲፬፥፲፫). የጌታ እረፍት የክብሩ ሙላት ነው, ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፬.