መበደል መለኮታዊ ህግን መተላለፍ፣ ኃጢያት መስራት፣ ወይም ችግር ወይም ጉዳት እንዲገኝ ማድረግ ነው፤ ደግሞም ማስከፋት ወይም ማናደድ ነው። የተበደለ ወንድም እንደ ጸናች ከተማ ጽኑ ነው, ምሳ. ፲፰፥፲፱. ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት, ማቴ. ፭፥፳፱. ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር, ማቴ. ፲፰፥፮ (ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፲፱–፳፪). ወንድሞቻችሁ ወይም እህቶቻችሁ ቢያስቀይሟችሁ፣ ከተናዘዘ ወይም ከተናዘዘችም ትታረቃላችሁ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፹፰. የእርሱ እጅ እንዳለበት ከማይመሰክሩ እና ትእዛዙን ከማያከብሩ በቀር፣ በምንም ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም፣ ወይም በማንም ላይ ቁጣው አይቀጣጠልም, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳፩.