ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች
የኋለኛው ቀን መለኮታዊ ራዕያትና የተነሳሱ አዋጆች መፅሐፍ። ጌታ እነዚህን የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ በእነዚህ በመጨረሻ ቀናት ለመመስረት እና ለማስተዳደር ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለተለያዩ የእርሱ ምትኮች ሰጠ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ይፋ ከሆኑት የቤተክርስቲያኗ ጽሁፎች ከመጸሐፍ ቅዱስ፣ ከመጸሐፈ ሞርሞን፣ እና የታላቅ ዋጋ ዕንቁ መካከል አንዱ ነው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ግን ልዩ ነው፣ ምክንያቱም ይህ የጥንት መዝገብ ትርጉም አይደለም፣ ጌታ እነዚህን ራዕዮች እርሱ ለመረጣቸው ነቢያት በእዚህ ዘመን መንግስቱን በዳግም ለመመስረት መሰረት የሰጣቸው ናቸው። በራዕዮች ውስጥ ሰው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለስላሳ ቢሆንም ፅኑ የሆነውን ድምፅ ይሰማል (ት. እና ቃ. ፲፰፥፴፭–፴፮)
የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚለው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች በእነዚህ የመጨረሻው ቀኖች የቤተክርስቲያኗ መሰረት፣ እና ለአለምም ጥቅም ነው (ት. እና ቃ. ፸፥ማስተዋወቂያ)። በውስጡ ያሉት ራዕዮች አለም ከተጀመረች ጊዜ ጀምሮ በነቢያት የተነገሩትን ቃላት በማሟላት ለጌታ ዳግም ምፅዓት መንገድ የሚዘጋጅበት ስራን ያስጀምራሉ።