ኤፍሬም
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የዮሴፍና የአስናት ሁለተኛ ልጅ (ዘፍጥ. ፵፩፥፶–፶፪፤ ፵፮፥፳)። በባህል የሚደረገውን በመቃረን፣ ምሳሌ ሳይሆን ኤፍሬም የብኩርነት በረከትን ተቀበለ (ዘፍጥ. ፵፰፥፲፯–፳)። ኤፍሬም የኤፍሬም ጎሳ አባት ሆነ።
የኤፍሬም ጎሳ
ኤፍሬም የእስራኤል ብኩርና ተሰጠው (፩ ዜና ፭፥፩–፪፤ ኤር. ፴፩፥፱)። በመጨረሻው ቀናት እድላቸው እና ሀላፊነታቸው ክህነትን ለመሸከም፣ ዳግም የተመለሰውን ወንጌል በአለም ለመውሰድ፣ እና ለተበተነው እስራኤል ምልክት ማንሳት ነው (ኢሳ. ፲፩፥፲፪–፲፫፤ ፪ ኔፊ ፳፩፥፲፪–፲፫)። በመጨረሻው ቀናት ከሰሜን ሀገሮች የሚመለሱትን የኤፍሬም ልጆች የክብር አክሊል ይሰጧቸዋል (ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፳፮–፴፬)።
የዮሴፍ ወይም የኤፍሬም በትር
በ ፮፻ ም.ዓ. ከኢየሩሳሌም ወደ አሜሪካ ተመርተው የሄዱ ከኤፍሬም ጎሳዎች ቡድን አንዱ መዝገብ። ይህ የቡድን መዝገብ የኤፍሬም ወይም የጆሴፍ በትር፣ ወይም መፅሐፈ ሞርሞን ተብሎ ይጠራል። ይህ እና የይሁዳ በትር (መፅሐፍ ቅዱስ) የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ የትንሳኤውን፣ እና በእነዚህ ሁለት የእስራኤል ቤት ክፍሎች መካከል የነበረ መለኮታዊ ስራውን በአንድነት ምስክር ይሰጣሉ።