አለማመን ደግሞም እምነት፣ ማመን ተመልከቱ በእግዚአብሔር እና በወንጌሉ እምነት ማጣት። በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም, ማቴ. ፲፫፥፶፰. በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም, ማቴ. ፲፯፥፲፬–፳፩. አለማመኔን እርዳው, ማር. ፱፥፳፫–፳፬. ኢየሱስ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ, ማር. ፲፮፥፲፬. የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን, ሮሜ ፫፥፫. አንድ አገር እምነት በማጣት ከሚመነምንና ከሚሞት አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል, ፩ ኔፊ ፬፥፲፫. የሚክዱበት ቀን ከመጣ፣ እንዲበተኑ እና እንዲጠፉ ያደርጋል, ፪ ኔፊ ፩፥፲–፲፩ (ት. እና ቃ. ፫፥፲፰). ባለማመናቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሊረዱት አልቻሉም ነበር, ሞዛያ ፳፮፥፩–፭. ስለማያምኑ እንደዚህ የሆነ ታላቅ ተአምራት ላሳያቸው አልቻልኩም, ፫ ኔፊ ፲፱፥፴፭. አዕምሮአችሁ ባለማመን ምክንያት ጨልሞባችሁ ነበር, ት. እና ቃ. ፹፬፥፶፬–፶፰.