ደቀ መዛሙርት ደግሞም ሐዋሪያ; መቀየር፣ የተቀየረ; ቀንበር; ክርስቲያኖች ተመልከቱ ክርስቶስ ባስተማረው መሰረት የሚኖር የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ (ት. እና ቃ. ፵፩፥፭)። ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ በስጋዊ አገልግሎቱ ጊዜ የጠራቸውን አስራ ሁለት ሐዋሪያትን ለመግለፅ ተጠቅመውበታል (ማቴ. ፲፥፩–፬)። ደቀ መዛሙርትም በኔፋውያንና በላማናውያን መካከል ቤተክርስቲያኑን እንዲመሩ ኢየሱስ የመረጣቸውን አስራ ሁለት ወንዶችን ለመግለፅም ተጠቅመውበታል (፫ ኔፊ ፲፱፥፬)። በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ሕጉን አትም, ኢሳ. ፰፥፲፮. እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ, ዮሐ. ፰፥፴፩. ሞርሞን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነበር, ፫ ኔፊ ፭፥፲፪–፲፫. እናንተ የእኔ ደቀመዛሙርት ናችሁ, ፫ ኔፊ ፲፭፥፲፪. ሶስቱ ደቀ መዛሙርት ሞትን አይቀምሱም, ፫ ኔፊ ፳፰፥፬–፲. እኔ በመረጥኳቸው ደቀመዛሙርቶቼ አፍ፣ የማስጠንቀቂያው ድምጽ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፩፥፬. ደቀ መዛሙርቴ በተቀደሰ ቦታ ላይ ይቆማሉ, ት. እና ቃ. ፵፭፥፴፪. በሁሉም ነገሮችም ድሀውን እና ችግረኛውን፣ የታመመውን እና የተሰቃየውን የማያስታውሱ ደቀ መዛሙርቴ አይደለም, ት. እና ቃ. ፶፪፥፵. ለእኔ ህይወቱን ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነውም ደቀመዛሙርቴ አይደለም, ት. እና ቃ. ፻፫፥፳፯–፳፰.