የጥናት እርዳታዎች
በዓለ ኀምሳ


በዓለ ኀምሳ

እንደ ሙሴ ህግ ክፍል፣ በዓለ ኀምሳ ወይም የመጀመሪያ ፍሬዎች ከፋሲካ ሀምሳ ቀናት በኋላ የሚከበር ነበር (ዘሌዋ. ፳፫፥፲፮)። በዓለ ኀምሳ የአዝመራ ወቅት በዓል ነበር፣ እናም በብሉይ ኪዳን ውስጥ የመከር በዓል ወይም የሰባቱ ሱባዔ በዓል ተብሎ ይታወቅ ነበር። ሐዋሪያቱ በኢየሩሳሌም ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉበት እና በልሳን የተናገሩበት ጊዜ የሚከበረው በዓል ይህ ነበር (የሐዋ. ፪ት. እና ቃ. ፻፱፥፴፮–፴፯)።