የመጨረሻ ቀናት፣ የኋለኛው ቀናት ደግሞም የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት; የጊዜዎች ምልክቶች ተመልከቱ አሁን የምንኖርባት ዘመን። ከጌታ ዳግም ምፅዓት በፊት ያሉ ቀናት (ዘመን)። በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እነግራችኋለሁ, ዘፍጥ. ፵፱፥፩. የሚቤዠኝ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ ይቆማል, ኢዮብ ፲፱፥፳፭. በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ይመሰረታል, ኢሳ. ፪፥፪. በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን ይመጣል, ፪ ጢሞ. ፫፥፩–፯. በመጨረሻው ቀን የሚያሾፉት ዳግም ምፅዓትን ይክዳሉ, ፪ ጴጥ. ፫፥፫–፯. እኔ የመጨረሻውን ቀን በተመለከተ እተነብይላችኋለሁ, ፪ ኔፊ ፳፮፥፲፬–፴. በመጨረሻ ቀናትም በዚህ፣ እንዲሁም በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ ስም ነው ቤተክርስቲያኔ የምትጠራው, ት. እና ቃ. ፻፲፭፥፬. ክርስቶስ በመጨረሻው ቀናት፣ ይመጣል, ሙሴ ፯፥፷.