ጦርነት ደግሞም ሰላም ተመልከቱ ትግል ወይም መዋጋት፤ በጦር መሳሪያ መዋጋት። ጌታ ጦርነትን የሚፈቅደው ቅዱሳኑ ቤተሰባቸውን፣ ንብረታቸውን፣ መብታቸውን፣ እድላቸውን፣ እና ነጻነታቸውን እንዲጠብቁ ብቻ ነው (አልማ ፵፫፥፱፣ ፵፭–፵፯)። ሞሮኒ የህዝቡን፣ መብቶቹን፣ ሀገሩን፣ እና ሀይማኖቱን ለመጠበቅ ፈለገ, አልማ ፵፰፥፲–፲፯. ጆሴፍ ስሚዝ ስለጦርነት ራዕይ እና ትንቢት ተቀበለ, ት. እና ቃ. ፹፯. ጦርነትን አስወግዱና ሰላም አውጁ, ት. እና ቃ. ፺፰፥፲፮፣ ፴፬–፵፮. ሰዎች እራሳቸውን፣ ጓደኞቻቸውን፣ እና ንብረትን በመጠበቅ ጥፋተኞች እንደማይሆኑ እናምናለን, ት. እና ቃ. ፻፴፬፥፲፩. በህግ በመታዘዝ፣ በማክበርና በመደገፍ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፪.