በጎ ድርገት ደግሞም ምፅዋት፣ የምፅዋት ስጦታ; በኩራት; አገልግሎት; ደሀ; ጾም፣ መጾም ተመልከቱ የሰዎችን መንፈሳዊ እና ምድራዊ ፍላጎቶችን ለመጠበቅ የሚደረግበት መንገድ ወይም ሁኔታ። በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረውም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ, ዘዳግ. ፲፭፥፲፩. ለድሀ የሚሰጥ አያጣም, ምሳ. ፳፰፥፳፯. እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ, ኢሳ. ፶፰፥፮–፯. ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል። ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት, ማቴ. ፳፭፥፴፭–፵. ፍላጎት ላላቸው ቁሳቁሳችሁን ትሰጧቸዋላችሁ, ሞዛያ ፬፥፲፮–፳፮. እንደፍላጎታቸውና ፈቃዳቸው አንዱ ለሌላው በአለማዊና መንፈሳዊ አመለካከት ያላቸውን ተካፈሉ, ሞዛያ ፲፰፥፳፱. እግዚአብሔርን ለማያውቁት ነፍሳት ደህንነት እንዲፆሙና እንዲፀልዩ ታዘዋል, አልማ ፮፥፮. ለደህንነታችሁ፣ እናም ደግሞ በዙሪያችሁ ላሉት ደህንነት ባለማቋረጥ ጸልዩ, አልማ ፴፬፥፳፯–፳፰. ሁሉም ነገሮች በጋራ ነበሩአቸው, ፬ ኔፊ ፩፥፫. ድሆችን አስታውሱ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፴–፴፩. ደሀዎችንና ችግረኞችን አገልግሏቸው, ት. እና ቃ. ፵፬፥፮. በሁሉም ነገሮችም ድሀውን እና ችግረኛውን አስታውሱ, ት. እና ቃ. ፶፪፥፵. ንብረታችሁን ለድሀዎች የማትሰጡት እናንተ ሀብታሞች ወዮላችሁ፣ እናም በስግብግብነት የሞላችሁና፣ በእጆቻችሁ የማትሰሩት ድሀ ሰዎችም ወዮላችሁ, ት. እና ቃ. ፶፮፥፲፮–፲፯. በፅዮን መካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም, ሙሴ ፯፥፲፰.