የጥናት እርዳታዎች
የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.)


የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.)

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) የጀመረው የንጉስ ጄምስ ትርጉም መፅሐፍ ቅዱስ ግምገማ ወይም ትርጉም። በእግዚአብሔር እንዲተረጉም እና ይህን እንደ ነቢይ ጥሪው ክፍል እንዲመለከተው ታዝዞ ነበር።

ምንም እንኳን ጆሴፍ አብዛኛውን ትርጉም በሐምሌ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ቢፈጽማቸውም፣ በ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ውስጥ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ጽሁፎችን ለማሳተም እያዘጋጀ ለውጦችን እያስተካከለ ነበር። ምንም እንኳን በህይወቱ ጊዜ የትርጉሙ ክፍሎችን ቢያትምም፣ ስራውን በሙሉ ለማተም በህይወት ቢኖር ኖሮ ተጨማሪ ቅያሬዎችን ማድርግ ይችል ይሆን ነበር። እንደገና የተደራጀው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የጆሴፍ ስሚዝ የተነሳሳ ትርጉም የመጀመሪያ ቅጂን በ፲፰፻፷፯ (እ.አ.አ.) አሳተሙ። ከእዚያም ጊዜ በኋላ ብዙ ቅጂዎች አሳትመዋል።

ነቢዩ በትርጉሙ ጊዜ ብዙ ነገሮችን ተምሯል። ብዙዎቹ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍሎችን (ለምሳሌ ት. እና ቃ. ፸፮፸፯፺፩፻፴፪) የተቀበለው በትርጉም ስራው ምክንያት ነው። ደግሞ፣ ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የተመዘገቡትን ልዩ መመሪያዎች ለጆሴፍ ሰጠ (ት. እና ቃ. ፴፯፥፩፵፭፥፷–፷፩፸፮፥፲፭–፲፰፺፥፲፫፺፩፺፬፥፲፻፬፥፶፰፻፳፬፥፹፱)። አሁን በታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ የሚገኙት መፅሐፈ ሙሴ እና የጆሴፍ ስሚዝ ማቴዎስ ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የተወሰዱ ናቸው።

የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጠፍተው የነበሩትን ግልፅ እና ውድ ነገሮችን ዳግሞ መልሷል (፩ ኔፊ ፲፫)። ምንም እንኳን ይህ የቤተክርስያኗ ህጋዊ መፅሐፍ ቅዱስ ባይሆንም፣ ይህ ትርጉም ብዙ አስደናቂ አስተያየቶችን ያቀርባል እናም መፅሐፍ ቅዱስን በማስተዋል ታላቅ ዋጋ ያለው ነው። ይህም ደግሞ ስለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ መለኮታዊ ጥሪና አገልግሎት ምስክር ነው።