ወንድሞች፣ ወንድም ደግሞም ሰው፣ ሰዎች; ሴት፣ ሴቶች; እህት ተመልከቱ እንደ ሰማይ አባታችን ልጆች፣ ወንዶች እና ሴቶች ሁሉ መንፈሳዊ መንድሞችና እህቶች ናቸው። በቤተክርስትያኗ ውስጥ፣ ወንድ አባላት እና የቤተክርስትያኗ ጓደኞች ብዙ ጊዜ ወንድም ተብለው ይጠራሉ። አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና, ሉቃ. ፳፪፥፴፪. ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል, ፩ ዮሐ. ፫፥፲–፲፯. ወንድሞቻችሁን እንደ እራሳችሁ አስቡባቸው, ያዕቆ. ፪፥፲፯. እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን እንደ እራሱ ይመልከት, ት. እና ቃ. ፴፰፥፳፬–፳፭. በንግግራችሁ በሙሉ ወንድሞቻችሁን አጠናክሩ, ት. እና ቃ. ፻፰፥፯.