መቆጠር ደግሞም ማክበር; ክብር ተመልከቱ ሰውን ወይም አንድ ነገርን፣ በተለይ በወንጌል አስተያየት፣ ብቁነት እና ዋጋ እንዳለው መመልከት። ከሰውም የተጠላ ነው፣ እኛም አላከበርነውም, ኢሳ. ፶፫፥፫–፬. በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነው, ሉቃ. ፲፮፥፲፭. እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር, ፊልጵ. ፪፥፫. ጌታ ሁሉንም ሕዝብ በአንድ ዐይን ይመለከታል, ፩ ኔፊ ፲፯፥፴፭. እያንዳንዱ ሰው ጎረቤቱን እንደራሱ ያክብር ዘንድ ጥብቅ ትዕዛዝ ነበር, ሞዛያ ፳፯፥፬ (ት. እና ቃ. ፴፰፥፳፬–፳፭). በሰላም ቀናቸው ምክሬን ትንሽ ዋጋ እንዳለው ተመለከቱት, ት. እና ቃ. ፻፩፥፰.