የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች ደግሞም መፅሐፈ ሞርሞን; ምስክር ተመልከቱ ጌታ ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በተጨማሪ ሌሎችን ስለመፅሐፈ ሞርሞን መለኮታዊነት ምስክር እንዲሰጡ አዘዘ (ት. እና ቃ. ፲፯፤ ፻፳፰፥፳)። የእነዚህን ምስክሮች ቃላት በመፅሐፈ ሞርሞን መጀምሪያ ገጾች “በመግቢያው” ውስጥ ተመልከቱ። በሶስት ሰዎች ቃል ቃሌን አፀናለሁ, ፪ ኔፊ ፲፩፥፫. ምስክሮች ለሰዎች ልጆች የእርሱን ቃል ምስክርነት ይሰጣሉ, ፪ ኔፊ ፳፯፥፲፪–፲፫. በሦስት ሰዎች አንደበት፣ እነዚህ ነገሮች ይፀናሉ, ኤተር ፭፥፬. በእምነት ሶስቱ ምስክቶች ሰሌዳዎችን ያያሉ, ት. እና ቃ. ፲፯.