የጥናት እርዳታዎች
በኣል


በኣል

በፈኒሽያ ውስጥ ዋና የሚመለክ ወንድ የጸሀይ አምላክ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፴፩)፣ ነገር ግን በተለያዩ ቦታዎች በተለያየ መንገድ የሚመለክ፥ በሞዓባውያን እንደ ብዔልፌጎር (ዘኁል. ፳፭፥፩–፫)፣ በሴኬም እንደ ኣልብሪት (መሳ. ፰፥፴፫፱፥፬)፣ በአቃሮን እንደ ብዔልዜቡል (፪ ነገሥ. ፩፥፪)። በኣል ከባቢሎን ቤል እና ከግሪክ ዘስ ጋር አንድ ይሆን ይሆናሉ። በኣል የሚለው ቃል በጌታ እና በባሪያው ጋር ያለውን ግንኙነት ይገልጻል። የበኣል ምልክት በልምድ ኮርማ በሬ ነበር። አስታሮት ከበኣል ጋር አብራ የምትመለክ አምላክ ነበረች።

በኣል፣ እንደሚመለክበት ቦታ ወይም እንደ በኣል አይነት ጸባይ እንዳለው ሰው አይነት፣ ከበአል ጋር ያለውን ግንኙነት ለማመከት አንዳንዴ ከሌላ ስም ወይም ቃል ጋር ይጣመር ነበር። በኋላም፣ በኣል በጣም ክፉ የሆነ ትርጉም እያለው ሲመጣ፣ ቡስቴ የሚባለው ቃል በበሚጣመርበት ስሞች ላይ ቦታውን ወሰደ። ቡስቴ ማለት “እፍረት” ማለት ነው።