ጥሪ፣ በእግዚአብሔር መጠራት፣ የተጠራበት ደግሞም መምረጥ፣ መረጠ፣ የተመረጠ (ግስ); መሾም፣ ሹመት; መጋቢ፣ መጋቢነት; ስልጣን; የተመረጠ (ቅጽል ወይም ስም) ተመልከቱ በእግዚአብሔር መጠራት ከእርሱ ወይም በእርሱ በተገቢ ስርዓት ስልጣን በተሰጣቸው የቤተክርስትያን መሪዊች በልዩ ሁኔታ እንዲያገለግሉት ምደባን ወይም ጋብዣን መቀበል ነው። እጁን በላዩ ጫነበት፣ አዘዘውም, ዘኁል. ፳፯፥፳፫. ነቢይ እንድትሆን ሹመት ሰጥቼሀለሁ, ኤር. ፩፥፭. እኔ መረጥኋችሁ እናም ሾምኋችሁ, ዮሐ. ፲፭፥፲፮. ጳውሎስ ሐዋርያ እንዲሆን ተጠርቶ ነበር, ሮሜ ፩፥፩. በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም, ዕብ. ፭፥፬. ኢየሱስ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ, ዕብ. ፭፥፲. በራዕይና በትንቢት መንፈስ መሰረት በእዚህ ህዝብ ሁሉ መካከል የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ተጠርቻለሁ, አልማ ፰፥፳፬. ቄሶች ከአለም መመስረት በፊት ተጠርተውና ተዘጋጅተው ነበር, አልማ ፲፫፥፫. እግዚአብሔርን ለማገልገል ፍላጎት ካለህ፣ ተጠርተሀል, ት. እና ቃ. ፬፥፫. በጠራሁ ስራ ጸንተህ ቁም, ት. እና ቃ. ፱፥፲፬. እስከምትጠራ ድረስ ለመስበክ እንደተጠራህ አታስብ, ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፭. ሽማግሌዎች የተመረጡትን ለመሰብሰብ ተጠርተዋል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፯. ካልተሾመ በስተቀር ማንም ወንጌሌን ለመስበክ ወይም ቤተክርስቲያኔን ለመግንባት አይችልም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፩. ብዙዎች ተጠርተዋል፣ ነገር ግን የተመረጡት ትንሽ ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፬. ሰው በእግዚአብሔር መጠራት አለበት, እ.አ. ፩፥፭.