ሳሌም ደግሞም መልከ ጼዴቅ; ኢየሩሳሌም ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መልከ ጼዴቅ የገዛት ከተማ። በዚህ ቀን በኢየሩሳሌም ቦታ ላይ የምትገኝ ይሆን ነበር። ሳሌም በእብራውያን ቋንቋ “ሰላም” ከሚለው ቃል ጋር የምትመሳሰል ነች። የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ, ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰. የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር, ዕብ. ፯፥፩–፪. መልከ ጼዴቅ የሳሌም ምድር ሁሉ ንጉስ ነበር, አልማ ፲፫፥፲፯–፲፰.