ያዕቆብ፣ የጌታ ወንድም
በአዲስ ኪዳን ውስጥ የጌታ (ገላ. ፩፥፲፱) እና ዮሳ፣ የስምዖን፣ የይሁዳ፣ እና የአንዳንድ እህቶች ወንድም (ማቴ. ፲፫፥፶፭–፶፮፤ ማር. ፮፥፫፤ ይሁዳ ፩፥፩)። እርሱም ትክክለኛው ያዕቆብ ተብሎ ይታወቅ ነበር እናም በኢየሩሳሌም ቤተክርስትያን ውስጥ አስፈላጊ ቦታ የያዘም ነበር (የሐዋ. ፲፪፥፲፯፤ ፲፭፥፲፫፤ ፩ ቆሮ. ፲፭፥፯፤ ገላ. ፪፥፱–፲፪)። ምናልባት የያዕቆብ መልእክትን የጻፈው እርሱ ነው።
የያዕቆብ መልእክት
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያለ መፅሐፍ። በመጀመሪያ ይህ የተጻፈው በውጪ ለተበተኑት ለአስራ ሁለቱ የእስራኤል ጎሳዎች ነበር እና የተጻፈውም ምናልባት በኢየሩሳሌም ነበር። መልእክቱ ስለተግባራዊ ሀይማኖት በግልፅ የተጻፉ ነገሮች ነበሩት፣ በእዚህም ተጨማሪ በምዕራፍ ፩ ውስጥ ሰው እውቀት ካጣ፣ እግዚአብሔርን ለእርዳታ እንዲጠይቅ አስፈላጊ ምክር የሚሰጥም ነበር (ያዕ. ፩፥፭–፮፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፱–፳)። ምዕራፍ ፪ ስለእምነት እና ስራ ይናገራል። ምዕራፍ ፫–፬ ምላስን ስለመቆጣጠር አስፈላጊነት ይናገራሉ እናም ቅዱሳን እርስ በራስ ክፉ እንዳይነጋገሩ ይገስጻሉ። ምዕራፍ ፭ ቅዱሳን ትእግስት እንዲኖራቸው እና ሲታመሙ ሽማግሌዎችን ለበረከት እንዲጠሩ ያበረታታል፤ ደግሞም ሌሎችን ለመቀየር መርዳት ስላለው በረከት ያስተምራል።