የመንፈስ ስጦታዎች ደግሞም ስጦታ ተመልከቱ ብቁ ለሆኑ ግለሰቦች ለእራሳቸው ጥቅምና ሌሎችን ለመባረክ እንዲጠቀሙበት፣ ጌታ የሚሰጠው ልዩ መንፈሳዊ በረከቶች። ለመንፈስ ስጦታዎች ልዩ መግለጫ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፮፥፲፩–፴፫፤ ፩ ቆሮ. ፲፪፥፩–፲፪፤ ሞሮኒ ፲፥፰–፲፰ አጥኑ። የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ, ፩ ቆሮ. ፲፪፥፴፩ (፩ ቆሮ. ፲፬፥፩). ኔፋውያን ብዙ የመንፈስ ስጦታዎች ተሰጥቷቸዋል, አልማ ፱፥፳፩. ጌታ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አይሰራም ለሚል ወዮለት, ፫ ኔፊ ፳፱፥፮. እግዚአብሔር ለታማኝ ስጦዎችን ይሰጣል, ሞር. ፱፥፯. ስጦታዎች በክርስቶስ መንፈስ ይሰጣሉ, ሞሮኒ ፲፥፲፯. ፲፩ ብዙ ስጦታዎች ስላሉ፣ እያንዳንዱም ሰው አንድ ስጦታ በእግዚአብሔር መንፈስ ተስጥቶታል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፲፩. የቤተክርቲያኗ መሪዎች ስጦታዎችን ለይተው እንዲያውቁ ተሰጥቷቸዋል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፳፯. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኗ መሪ የሚሰጣቸው ስጦታዎች በሙሉ አሉት, ት. እና ቃ. ፻፯፥፺፩–፺፪.