የጥናት እርዳታዎች
መና


መና

የማር ጣም ያለው ትንሽ፣ ክብ የመሰለ ምግብ (ዘፀአ. ፲፮፥፲፬–፴፩) ወይም አዲስ ዘይት (ዘኁል. ፲፩፥፯–፰)። በምድረበዳ ውስጥ በነበሩበት በአርባ አመታት ጊዜ ጌታ የእስራኤል ልጆችን ለመመገብ ይህን ሰጣቸው (ዘፀአ. ፲፮፥፬–፭፣ ፲፬–፴፣ ፴፭ኢያ. ፭፥፲፪፩ ኔፊ ፲፯፥፳፰)።

የእስራኤል ልጆች መና (ወይም በዕብራውያን ቋንቋ ማን-ሁ) ብለው ጠሩት—ይህም “ምንድን ነው?” ማለት ነው—ምክያቱም ምን እንደሆነ አላወቁምና (ዘፀአ. ፲፮፥፲፭)። ደግሞም ይህ “የመላእክት ምግብ” እና “የሰማይ እንጀራ” ተብሎ ይታወቃል (መዝ. ፸፰፥፳፬–፳፭ዮሐ. ፮፥፴፩)። ይህም የህይወት እንጀራ የሚሆነው የክርስቶስ ምሳሌ ነበር (ዮሐ. ፮፥፴፩–፴፭)።