መስቀል
ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት እንጨት (ማር. ፲፭፥፳–፳፮)። አሁን በአለም ውስጥ ብዙዎች ይህን እንደ ክርስቶስ መሰቀልና ስለኃጢያት ዋጋ መክፈሉ ምልክት አድርገው ያስቡበታል፤ ነገር ግን ጌታ ለተሰቀለበትና ለመስዋዕቱ የእራሱን ምልክት መስርቷል—ይህም የቅዱስ ቁርባን ዳቦና ውሀ ነው (ማቴ. ፳፮፥፳፮–፳፰፤ ት. እና ቃ. ፳፥፵፣ ፸፭–፸፱)። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ መስቀላቸውን የሚያነሱ ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ወድደው ኃጢያተኝነታቸውንና ምድራዊ ፍላጎታቸውን ይክዳሉም፣ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ያከብራሉ(ጆ.ስ.ት.፣ ማቴ. ፲፮፥፳፭–፳፮ [ተጨማሪ])።