የጥናት እርዳታዎች
መንፈሳዊ ሞት


መንፈሳዊ ሞት

ከእግዚአብሔር እና ከተፅዕኖው መለየት፤ ጻድቅን ከሚነኩ ነገሮች መሞት። ሉሲፈር እና ከሰማይ ሰራዊት አንድ ሶስተኞቹ ከሰማይ በሚወረወሩበት ጊዜ በመንፈስ ሞቱ (ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፮–፴፯)።

መንፈሳዊ ሞት ወደ አለም የተዋወቀው በአዳም ውድቀት ምክንያት ነው (ሙሴ ፮፥፵፰)። ክፉ ሀሳቦች፣ ቃላት፣ እና ስራዎች ያላቸው ስጋዊ ሰዎች በምድር ላይ በህይወት እያሉ በመንፈስ የሞቱ ናቸው(፩ ጢሞ. ፭፥፮)። በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ በኩል እና ለወንጌሉ መሰረታዊ መርሆችና ስነስርዓቶች ታዛዥ በመሆን፣ ወንዶች እና ሴቶች ከኃጢያት ንጹህ ለመሆንና መንፈሳዊ ሞትን ለማሸነፍ ይችላሉ።

መንፈሳዊ ሞት ደግሞም የስጋዊ ሰውነት ሞትን በመከተል ለደርስ ይችላል። ከሞት የተነሱ ሰዎች እና ዲያብሎስና መላእክቱ ይፈረድባቸዋል። በወንጌሉ ብርሀን እና እውነት ላይ በፈቃደኝነት የሚያምጹ በመንፈሳዊ ሞት ይሰቃያሉ። ይህ ሞት ብዙም ጊዜ ሁለተኛ ሞት ይባላል (አልማ ፲፪፥፲፮ሔለ. ፲፬፥፲፮–፲፱ት. እና ቃ. ፸፮፥፴፮–፴፰)።