ኪምባል፣ ስፔንሰር ደብሊው ደግሞም አስተዳደሪያዊ አዋጅ ፪ ተመልከቱ ቤተክርስቲያኗ በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ከተመሰረተች በኋላ አስራ ሁለተኛው ፕሬዘደንት። ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል ከ፲፱፻፸፫ እስከ ፲፱፻፹፭ (እ.አ.አ.) እንደ ፕሬዘደንት አገለገሉ። የተወለዱት በ፲፰፻፺፭ (እ.አ.አ.) ነበር እና በ፺ አመታቸው በ፲፱፻፹፭ (እ.አ.አ.) ሞቱ። በሰኔ ፲፱፻፸፰ (እ.አ.አ.)፣ ቀዳሚ አመራር የክህነት መብትን እና የቤተመቅደስ በረከቶችን ብቁ ለሆኑ ወንዶች ሁሉ የሚዘረጋ ራዕይ ፕሬዘደንት ኪምባል እንደተቀበሉ አስታወቀ, አ.አ. ፪.