ቃል ኪዳን
በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ስምምነት፣ ነገር ግን በስምምነቱ እንደ እኩል አይደሉም። እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ቅድመ ሁኔታን ይሰጣል፣ እናም ሰዎች እርሱ እንዲያደርጉ የሚጠይቃቸውን ለማድረግ ይስማማሉ። ከእዚያም እግዚአብሔር ሰዎችን አንዳንድ በረከቶች ለታዛዥነታቸው ቃል ይገባላቸዋል።
ሰረታዊ መርሆች እና ስነስርዓቶች የሚቀበሉት በቃል ኪዳን ነው። እንደዚህ አይነት ቃል ኪዳኖች የሚሰሩ የቤተክርስቲያን አባላት እነዚህን ለማክበር ቃል ይገባሉ። ለምሳሌ፣ አባላት በጥምቀት ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ እናም ቅዱስ ቁርባንን በመውሰድ ያን ቃል ኪዳን ያሳድሳሉ። ተጨማሪም ቃል ኪዳኖች በቤተመቅደስ ውስጥ ይሰራሉ። የጌታ ህዝቦች የቃል ኪዳን ህዝብ ናቸው እናም ከጌታ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች በሚያከብሩበት ጊዜ በይበልጥ ይባረካሉ።