የጥናት እርዳታዎች
ናታን


ናታን

በንጉስ ዳዊት ዘመን የነበረ የብሉይ ኪዳን ነቢይ። ለጌታ ቤተመቅደስ ለመገንባት ዳዊት ሀሳብ ሲያቀርብ፣ ጌታ ናታን ዳዊትን እንዳይገነባ እንዲነግረው አዘዘ። ናታን ዳዊት ከእርሱ ጀግናዎች አንዱ የሆነው የኦርዮ ሞት ምክንያት ስለሆነ እናም የኦርዮን ሚስት ቤርሳቤህ ስላገባ ገሰጸው (፪ ሳሙ. ፲፪፥፩–፲፭ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፴፰–፴፱)። ሳዶቅ፣ ከናታን ጋር፣ የዳዊትን ልጅ ሰለሞንን እንደ ንጉስ ቀቡ (፩ ነገሥ. ፩፥፴፰–፴፱፣ ፵፭)።