አጥቢያ ኮከብ ደግሞም ሲዖል; አፍራሽ; የክርስቶስ ተቃዋሚ; የጥፋት ልጆች; ዲያብሎስ ተመልከቱ ስሙ “የሚበራው” ወይም “ብርሀን ያዢው” ማለት ነው። እርሱ የንጋት ልጅ ተብሎ ይታወቃል። አጥቢያ ኮከብ የሰማይ አባት የመንፈስ ልጅ ነበር እናም በቅድመ ምድር ህይወት አመፅን መራ። የአጥቢያ ኮከብ ስም በመፅሐፍ ቅዱስ የሚገኘው አንድ ጊዜ ብቻ ነው (ኢሳ. ፲፬፥፲፪)። የኋለኛው ቀን ራዕይ ስለአጥቢያ ኮከብ መውደቅ ተጨማሪ ዝርዝር ይሰጣል (ት. እና ቃ. ፸፮፥፳፭–፳፱)። አጥቢያ ኮከብ በቅድመ ምድር ህይወት ወደቀ, ኢሳ. ፲፬፥፲፪ (ሉቃ. ፲፥፲፰; ፪ ኔፊ ፳፬፥፲፪). ከወደቀ በኋላ ሰይጣን እና ዲያብሎስ ሆነ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፳፭–፳፱ (ሙሴ ፬፥፩–፬).