አክሊል ደግሞም የዘለዓለም ህይወት ተመልከቱ በመሪዎች ጭንቅላት ላይ የሚቀመጥ ክብ ጌጣጌጥ። ይህም የሰለስቲያል ሀይል፣ ግዛት፣ እና አምላክነት ምልክት ሊሆንም ይችላል። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሁሉ በማክበር የሚጸኑት የዘለአለም ህይወት ዘውድን ይቀበላሉ። (ት. እና ቃ. ፳፥፲፬፤ ሙሴ ፯፥፶፮፤ ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፩ ተመልከቱ።) ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል, ፪ ጢሞ. ፬፥፰. የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ, ፩ ጴጥ. ፭፥፬. በእኔ የሞቱት ሙታን የጽድቅን አክሊል ይቀበላሉ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፲፫. በአባቴ ቤት ውስጥ አክሊል ይቀበላሉ, ት. እና ቃ. ፶፱፥፪. ጌታ ቅዱሳንን ለተዘጋጀላቸው አክሊል እንዲመጡ ያዘጋጃቸዋል, ት. እና ቃ. ፸፰፥፲፭. ጌታ ለቅዱሳኑ በቀኝ እጁ በኩል የክብር አክሊል ኪዳን ገብቶላቸዋል, ት. እና ቃ. ፻፬፥፯.