የተቀየሩ ሰዎች ጉዳትን ወይም ሞትን ወደ ዘለአለማዊነት በትንሳኤ እስከሚነሱ ድረስ እንዳይቀምሱ የተለወጡ ሰዎች። ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና, ዘፍጥ. ፭፥፳፬ (ዕብ. ፲፩፥፭; ት. እና ቃ. ፻፯፥፵፰–፵፱). እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴን መቃብር ማንም አላወቀም, ዘዳግ. ፴፬፥፭–፮ (አልማ ፵፭፥፲፱). ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ, ፪ ነገሥ. ፪፥፲፩. እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ, ዮሐ. ፳፩፥፳፪–፳፫ (ት. እና ቃ. ፯፥፩–፫). ሞትን በጭራሽ አትቀምሱም, ፫ ኔፊ ፳፰፥፯. ሞትን እንዳይቀምሱ፣ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ ተደርጓል, ፫ ኔፊ ፳፰፥፴፰ (፬ ኔፊ ፩፥፲፬; ሞር. ፰፥፲–፲፩). ተወዳጁ ዮሐንስ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ይኖራል, ት. እና ቃ. ፯. የሄኖክን ፅዮን ወደ እቅፌ የወሰድኩት እኔው ነኝ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፬ (ሙሴ ፯፥፳፩፣ ፴፩፣ ፷፱). ሔኖክ እና ወንድሞቹ እስከ ጽድቅ ቀን ድረስ የምቆጥባት ከተማ ናቸው, ት. እና ቃ. ፵፭፥፲፩–፲፪. ኤልያስ ሞትን ሳይቀምስ ወደሰማይ ተወሰደ, ት. እና ቃ. ፻፲፥፲፫. መንፈስ ቅዱስ በብዙዎች ላይ አረፈ፣ እና እነርሱም በሰማይ ሀይሎች ወደ ፅዮን አረጉ, ሙሴ ፯፥፳፯.